LIMSwiki
Appearance
ስድስት በተራ አቆጣጠር ከአምስት የሚከተለው ቁጥር ነው።
ምልክቱ ከግዕዝ እንደ ተወረሰ ፮ ነው፣ ይህም ከግሪክ አልፋቤት ቁጥር ፊደል ስቲግማ («ϛ») እንደ ተወሰደ ይታመናል።
በብዙ ልሳናት የሚገኘው ምልክት 6 ከሕንዳዊ ቁጥር ምልክቶች ተደረጀ። እነዚህ ምልክቶች በአውሮፓ ከ968 እና 1550 ዓም መካከል እየተደረጁ ተቀባይነት አገኙ። ከዚያ አስቀድሞ በሮማውያን ቁጥር ምልክቶች የ«ስድስት» ምልክት «VI» ነበር።