LIMSpec Wiki

ጳጉሜን

ጳጉሜን የወር ስም ሆኖ በነሐሴ እና በመስከረም ወራት መኻል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ የመጨረሻው እና አሥራ ሦስተኛው (፲፫ ኛው) የወር ስም ነው። «ጳጉሜን» በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዘመነ ዮሐንስ ሥግር ዓመት (በጎርጎርያዊ አቆጣጠር leap year) በመሆኑ ስድስት (፮) ዕለታት አሉት። በዘመነ ልቆስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና በዘመነ ማርቆስ አምስት (፭) ዕለታት አሉት።

«ጳጉሜን» የሚለው ስም ምንጩ ከግሪክ ቋንቋ ሲሆን <<ቀሪ ዕለታት>> ማለት ነው። [1] ነሐሴ የክረምት ሦስተኛው ወር ነው።

ኢትዮጵያ በአለም ብቸኛዋ የ13 ወራት ጸጋ ባለቤት ናት። ይህ የፓጉሜን ወር በኢትዮጵያውያን ዘንድ የምህረት ወር ተብሎ ይታመናል። ወደ አዲስ አመት መግቢያ (መሸጋገርያ) ወርም ነው።

ዘመን

  1. ዘመነ ማቴዎስ
  2. ዘመነ ማርቆስ
  3. ዘመነ ሉቃስ
  4. ዘመነ ዮሀንስ


ዋቢ ምንጮች

  1. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2014-03-31. በ2010-09-03 የተወሰደ.