Infrastructure tools to support an effective radiation oncology learning health system
Contents
0 | |
---|---|
ዜሮ/Zero |
ዜሮ ወይንም 0 ወይንም ፨ በቁጥር ጽሕፈት ወቅት የባዶነት ማመላከቻ ምልክት ነው። ዜሮ በራሱም ቁጥር ሲሆንም ያንድን መለኪያ ባዶነት ያመለክታል። ለምሳሌ የባዶ ስብስብ አባላት ቁጥር ዜሮ ነው እንላለን።
ታሪክ
የዜሮ ፅንሰ ሐሳብ በባቢሎኒያኖች የፈለቀ ሲሆን ይኼውም በ3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ነበር። ሆኖም ባቢሎኒያኖቹ ዜሮን እኛ እንደምንጠቀምበት ሳይሆን እንደ ቦታ ያዢ ምልክት ነበር የጠቀሙበት። ለምሳሌ 304፣ ወይንም 450 ሲጽፉ፣ 0 እዚህ ላይ የቁጥር አለመኖርንና ቦታ መያዝን ብቻ ያመላክታል።
ዜሮን እኛ በምንጠቀምበት መልኩ የተጠቀሙት ህንዶች ሲሆኑ ይሄውም ቢያንስ ከ620 ዓ.ም. ጀምሮ ነበረ።[1] ለህንዶች፣ ዜሮ ቦታ መያዣ ምልክት ብቻ ሳይሆን፣ እራሱን የቻለ ቁጥር ሲሆን ለስሌት የሚረዳ ነበር። በህንዶች ዘንድ 0 ለመደመር፣ ለመቀነስ፣ ለማካፈልና ለማባዛት ግልጋሎት ይውል ነበር።
ከ768 ዓም ጀምሮ አረቦች ከህንዶች የዚህን ቁጥር ጥበብ በመቅሰም ለአዲሱ ቁጥር ስፍር صفر የሚል ስያሜ ሰጡት። ትርጓሜውም ባዶ ማለት ነበር። የአረብ ሊቃውንት ከአውሮፓ ሊቃውንት በነዚህ ፪ መቶ አመታት በዜሮ (0) ጥቅም ቅድምትነታቸው ምክንያት፣ በሥነ ቁጥር ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሳይንስ ዘርፎች ሥነ ቁጥሮች በመቀለላቸው በኩል፣ ለጊዜው የአረብ አለም ሊቃውንት በይበልጥ ለመግፋት ቻሉ።
ከዚያ ቁጥሩ መጀመርያ በአውሮፓዊ መጽሐፍ የተጠቀሰው በ968 ዓም ነበር። ከአረቦቹ ይህን ቁጥር የቀሰመው ጣሊያኑ ፊቦናቺ «ስፍር» የሚለውን ወደ ዜፊሮ በመቀየር የቁጥሩ ጥቅም በተለይ በ12ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. አውሮጳ እንዲስፋፋ ሆነ። በኋላም በእንግሊዝኛ «ዜፊሮ» ወደ «ዜሮ» ተለውጦ ስሙ በዚህ ረጋ።
ዜሮና ሒሳብ
የዜሮ ጠባዮች
- መደመር: x + 0 = 0 + x = x. ዜሮን ሌላ ቁጥር ላይ መደመር ያን ቁጥር አይለውጥም
- መቀነስ: x − 0 = x and 0 − x = −x.
- ማባዛት: x · 0 = 0 · x = 0.
- ማካፈል: 0|x = 0, x እዚህ ላይ ዜሮ ያልሆነ ቁጥር ነው። በአንጻሩ x|0 ያልተተርጎመ ነው።
- ንሴት: x0 = x/x = 1, ይህ የማይሰራው x = 0 ሲሆን ብቻ ነው። በተጨማሪ ለማንኛው እውን ቁጥር x, 0x = 0.