FAIR and interactive data graphics from a scientific knowledge graph
Contents
የላይቤሪያ ሪፐብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: ኦል ሄል፣ ላይቤሪያ፣ ሄል! እንግሊዝኛ፦ All Hail, Liberia, Hail! |
||||||
ላይቤሪያ በቀይ ቀለም
|
||||||
ዋና ከተማ | ሞንሮቪያ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | እንግሊዝኛ | |||||
መንግሥት {{{ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት |
ጆርጅ ዌያ ጁወል ተይለር |
|||||
ዋና ቀናት ሐምሌ ፳ ቀን ፲፰፻፴፱ ዓ/ም (July 26, 1847 እ.ኤ.አ.) |
የነጻነት ቀን |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
111,369 (103ኛ) 13.514 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2008 እ.ኤ.አ. ግምት የ2005 እ.ኤ.አ. ቆጠራ |
3,489,072 (132ኛ) 3,482,211 |
|||||
ገንዘብ | የላይቤሪያ ዶላር1 | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +0 | |||||
የስልክ መግቢያ | 231 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .lr | |||||
1. የአሜሪካ ዶላርም በሰፊ ጥቅም ላይ ነው |
ላይቤሪያ (እንግሊዝኛ፦ Liberia)፣ በይፋ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ (እንግሊዝኛ፦ Republic of Liberia)፣ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በጊኒ፣ ኮት ዲቯር፣ ሴራሊዮን እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች። ላይቤሪያ የቅኝ ግዛት ሆና በ1822 እ.ኤ.አ. ከአሜሪካ በመጡ ነጻ የወጡ ባሪያዎች የተመሠረተች ሲሆን በአካባቢው ግን የተለያዩ ብሔሮች ለብዙ ምእተ አመታት ኖረዋል። መሥራቾቹ ዋና ከተማቸውን ሞንሮቪያ ብለው ለአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጄምስ ሞንሮው ሰይመውታል። ሐምሌ ፳ ቀን ፲፰፻፴፱ ዓ/ም ነጻነት አወጁና ግዛቷ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ሆነች። በ1980 እ.ኤ.አ. በወታደራዊ መፈንቅለ-መንግስት የላይቤሪያ አመራር ከወረደ በኋላ ከ1989 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ድረስ ሀገሩዋ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀሉና የሀገሩዋን ኢኮኖሚ ያቃወሱ ሁለት የእርስ-በርስ ጦርነቶችን አይታለች።
የስም አመጣጥ
«ላይቤሪያ» ከእንግሊዝኛው liberty (ሊበርቲ፣ ማለትም ነጻነት) ከሚለው ቃል ነው የመጣው።
ታሪክ
የምዕራብ አፍሪካ አገሬዎች (ተወላጆች)
የአንትሮፖሎጂ ምርምር እንደሚያሳየው ከሆነ፣ በላይቤሪያ ላይ ከ12ኛው ክፍለ-ዘመን ወይም ከዛ በፊት ጀምሮ ሰው ሠፍሯል። መንዴ (Mende) የሚባል ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ ምዕራብ ሲስፋፉ፣ ሌሎች ታናናሽ ብሄረሰቦችን ወደ ደቡብ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ገፍተዋቸዋል። ዴዪ፣ ባሳ፣ ክሩ፣ ጎላ እና ኪሲ የሚባሉ ጎሳዎች በአካባቢው ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደነበሩ በማስረጃ ይታወቃል። ይህ ፍልሰት የጨመረው የማሊ ግዛት በ1375 እ.ኤ.አ. እና የሶንጋይ ግዛት በ1591 እ.ኤ.አ. ሲዳከሙ ነው። በተጨማሪም ወደ ውስጥ ያለው ሥፍራ ወደ በርሃነት እየተለወጠ ስለመጣ፣ ነዋሪዎቹ ወደ እርጥቡ ፔፐር ጠረፍ (Pepper Coast) እንዲሄዱ ተገደዱ። ከማሊና ሶንጋይ ግዛቶች የመጡ አዳዲስ ነዋሪዎች ጥጥ ማሽከርከር፣ ልብስ መስፋት፣ ብረት ማቅለጥ እና ሩዝና ማሽላ ማብቀልን የመሳሰሉ ጥበቦች ለቦታው አስተዋወቁ።
መኔ ሰዎች (ከመንዴ ወታደሮች የመጡ) አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ ቫይ የሚባል የማሊ ግዛት ከፈረሰ በኋላ ለመሰደድ የተገደደ ብሔር ወደ ግራንድ ኬፕ ማውንት (Grand Cape Mount) የሚባለው ሥፍራ ፈለሱ። የክሩ ብሔር የቫይን ፍልሰት ተቃወሙ። ከመኔ ብሔር ጋር አንድ ላይ በመሆንም የቫይ ብሔርን ከግራንድ ኬፕ ማውንት አልፈው እንዳይስፋፉ አገዱ።
በጠረፍ ላይ የሚኖሩት ሰዎች ታንኳ ሰርተው ከካፕ-ቨርት እስከ የወርቅ ጠረፍ (Gold Coast) ድረስ ካሉት ሌሎች ምዕራብ አፍሪካውያን ጋር ይገበያዩ ነበር። የክሩ ጎሳ በመጀመሪያ ለአውሮፓውያን ሰው ያልሆኑ ነገሮችን ይሸጡ ነበር። ግን በኋላ በየአፍሪካ ባሪያ ንግድ ውስጥ መሳተፍ ጀመሩ።
የክሩ ሠራተኞች ቦታቸውን ትተው በትልቅ እርሻዎችና የግንባታ ሥራዎች ላይ ተሳትፈዋል። አንዳንዶቹም የስዊዝና ፓናማ መስኖዎች ለመገንባት ረድተዋል።
ሌላ ግሌቦ የሚባሉ ሰዎች የመኔ ጎሳ አካባቢያቸውን ሲወር፣ በኋላ የላይቤሪያ ወደ ሚሆነው ጠረፍ አመሩ።
የቀድሞ የአውሮፓውያን ግንኙነት
በ1461 እ.ኤ.አ. እና 17ኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ መካከል ፖርቱጋላዊ፣ ሆላንዳዊና ብራታንያዊ ነጋዴዎች በላይቤሪያ የንግድ ቦታ አቋቁመው ነበር። በተጨማሪም የአንድ የሚጥሚጣ አይነት ፍሬ በመብዛቱ ፖርቱጋላዊያን አካባቢውን Costa da Pimenta (ኮስታ ዳ ፒሜንታ) ማለትም የፍሬ ጠረፍ ብለው ሰይመውት ነበር።
ከአሜሪካ የመጡ ሰፋሪዎች
በ1822 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ የቅኝ መግዛት ማህበር ላይቤሪያን ባሪያ የነበሩ ጥቁር ሰዎች የሚላኩበት ቦታ አድርጎ አቋቋመ። ከሌሎች ባሪያ ያልነበሩ ጥቁር አሜሪካውያንም ወደ ላይቤሪያ ለመሄድ የመረጡ ነበሩ። ወደ እዛ የሄዱት አሜሪካዊ ላቤሪያዊያን በመባል ይታወቃሉ። በሐምሌ 20 ቀን 1839 ዓ.ም. እነዚህ ሰፋሪዎች የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ነፃነትን አወጁ።
የአመራር ክፍሎች
ቁጥር | የአገዛዝ ክፍል | የሕዝብ ብዛት (2008 እ.ኤ.አ.)[1] | ስፋት (ካሬ ኪ.ሜ.)[1] | የተፈጠረው (እ.ኤ.አ.) |
---|---|---|---|---|
1 | ቦሚ | 82,036 | 1942 | |
2 | ቦንግ | 328,919 | 8772 | 1964 |
3 | ግባርፖሉ | 83,758 | 9689 | 2001 |
4 | ግራንድ ባሳ | 224,839 | 7936 | |
5 | ግራንድ ኬፕ ማውንት | 129,055 | 5162 | |
6 | ግራንድ ጌዴህ | 126,146 | 10484 | 1964 |
7 | ግራንድ ክሩ | 57,106 | 3895 | 1984 |
8 | ሎፋ | 270,114 | 9982 | 1964 |
9 | ማርጊቢ | 199,689 | 2616 | |
10 | ሜሪላንድ | 136,404 | 2297 | 1857 |
11 | ሞንትሴራዶ | 1,144,806 | 1909 | 1847 |
12 | ኒምባ | 468,088 | 11551 | 1964 |
13 | ሪቨር ሴስ | 65,862 | 5594 | |
14 | ሪቨር ጂ | 67,318 | 5113 | 2000 |
15 | ሲኑ | 104,932 | 10137 | 1847 |
ሀይማኖት
አርባ ከመቶ የሚሆነው የሀገሩ ሕዝብ ክርስቲያን ነው። ሌላ ሀያ ከመቶ የሚሆን ሕዝብ የራሱ የአገሬው ሀይማኖት አለው። የቀረው አርባ ከመቶ ሕዝብ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው።
ትምህርት
የላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሞንሮቪያ ይገኛል። በ1862 እ.ኤ.አ. የተከፈተ ሲሆን ከአፍሪካ ቀደምት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱ ነው። በእርስ-በርስ ጦርነት ጊዜ በጣም የተጎዳ ሲሆን አሁን እንደገና እየተገነባ ነው።
ከቲንግተን ዩኒቨርሲቲ በየአሜሪካ ኢጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን በ1889 እ.ኤ.አ. ተመሥርቷል። ግቢው በሱዋኮኮ፣ ቦንግ የአገዛዝ ክፍል ይገኛል።
ነጥቦች
- ^ ሀ ለ "2008 National Population and Housing Census: Preliminary Results" (በእንግሊዝኛ). Government of the Republic of Liberia (2008). Archived from the original on 2012-02-13. በ2008-10-14 የተወሰደ.
|